አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ሊጠቀምበት የነበረ 218 ማዳበሪያ አደንዛዥ ዕጽ በሁመራ ግንባር ተይዞ መቃጠሉን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሜን ዳይሬክቶሬት ዲቪዥን 3 ኃላፊ ኮማንደር እንየው አለባቸው እንደገለጹት÷ አደንዛዥ ዕጹ የተያዘው ከሁመራ ወደ ሱዳን ሊሻገርና ተቀምሞ በዱቄት መልክ ለሽብር ቡድኑ አባላት መልሶ ለማሰራጨት ታስቦ እንደነበር ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
ይህም የተያዘው አደንዛዥ ዕጽ በተለያዩ ጊዜያት በፌደራል ፖሊስ እና በሌሎች የጸጥታ አካላት እንዲሁም በአካባቢው ማህበረሰብ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል መሆኑ ተገልጿል፡፡
የአሸባሪው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የቃጣውን ክህደትና የዘር ጭፍጨፋ ለማባባስ እንደትልቅ መሳሪያ እንደሚጠቀምበት ኃላፊው ጨመረው ገልጸዋል፡፡
በዕጽ ዝውውር ተግባር ላይ በተሳተፉ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሚገኝም ነው ኮማንደር እንየው የገለጹት፡፡
ከሱዳን ወደ ሁመራ በተናጠል አደዛዥ ዕጽ ይዘው ሰርገው ለመግባት እየሞከሩ ያሉ አካላትም በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከፌደራል ፖሊስ፣ ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከአማራ ክልል ልዩ ሃይል ጋር በጋራ የድንበር አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ላይ እንዳሉ መግለጻቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!