የሀገር ውስጥ ዜና

በጅማ ከተማ በህገወጥ መንገድ የተከማቸ መድሃኒት ተያዘ

By Alemayehu Geremew

September 22, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ ጄኔቫ በተባለ ሆቴል ከምድር በታችና በላይ በተገነቡ 3 ክፍሎች ውስጥ የተከማቸ መድሃኒት ተያዘ።

የከተማው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት የጤናና ጤና ነክ ቁጥጥር አስተባባሪ አቶ አክበር ከማል እንደገለፁት÷ ከዚህ ቀደም ጅማ መናኸሪያ አካባቢ ህገወጥ መድሃኒት እንደሚሸጥ ጥቆማ ሲደርሳቸው ነበር።

በጥቆማው መሰረት ሰሞኑን ከንግድ ጽህፈት ቤት ጋር በጥምረት የተቋቋመው ግብረ ኃይል ባደረገው ፍተሻ መድሃኒቶቹ መያዛቸውን ነው የተናገሩት።

በቀጣይም ከመድሃኒቱ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚደረጉ አቶ አክበር ገልፀዋል።

በሙክታር ጠሃ