አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በልዩ ልዩ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቻው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ውይይት ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ ወቅታዊ የጸጥታና የደኅንነት ሁኔታ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች፣እንዲሁም ጂኦፖለቲካዊ ለውጦችን የተመለከቱ አጀንዳዎች እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
አክለውም የሚታዩ ክፍተቶችን፣ ለውጥ የሚያስፈልጋቸውና መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር ገምግሞ በቀጣይ እንደ ሀገር መከናወን ስለሚገባቸው ተግባራት አቅጣጫዎች መቀመጡን ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!