የሀገር ውስጥ ዜና

የቱሪዝም ቀን በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው

By Meseret Awoke

September 22, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)”ቱሪዝም ለሁለተናዊ እድገት!” በሚል መሪ ቃል የዓለም አቀፉ የቱሪዝም ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ነው ።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ፋይዛ መሐመድ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በማዘጋጃ ቤት በመከበር ላይ ይገኛል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ42ኛ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ በሚከበረው የዓለም አቀፉ የቱሪዝም ቀን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 5 የሚከበር ይሆናል።

ቀኑ በከተማዋ የሚገኙ የቱሪስት መዳራሻ ስፍራዎችን የማስጎብኘት፣ በጎዳና ላይ ትርዒቶች፣ በስፖርት ቱሪዝም እና በመሳሰሉት ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ከከተማዋ ፕረስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!