Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በማይጠብሪ ግንባር ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ሲፋለሙ ለተሰው ወጣቶች የቀብር ስነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በማይጠብሪ ግንባር ሃገርን ላለማስደፈር ከሽብር ቡድኑ ህወሓት ጋር ሲፋለሙ ለተሰው ወጣቶች የቀብር ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የቀብር ስነ ስርዓት የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የሰማዕታት ቤተሰቦች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ወጣቶች የተሟላ ትጥቅ ሳይኖራቸው ወራሪውን የትህነግ ቡድን አንገት ላንገት ተናንቀው በጀግንነት መስዋዕት መሆናቸውም ተነስቷል።

በመላኩ ገድፍ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version