አዲስ አበባ፤ መስከረም 11፤ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ምድር ወረዳ ምንም እግር የሌላት የበግ ግልገል መወለዷ ተሰማ፡፡
በወረዳው ጉርሜ ቀበሌ ትናንት ምሽት ነው ሴት የበግ ግልገሏ የተወለደችው ፡፡
የወረዳው መንግስት ኮምዩንኬሽን ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሽፈራ ለማ÷አሁን ላይ ግልገሏ በመልካም ጤንነት ላይ ሆና ባለቤቶቹ እየተንከባከቧት ይገኛሉ ብለዋል።
በሳይንሱ እዲህ አይነት አፈጣጠር ይከሰታል ያሉት በሰሜን ሸዋ ዞን እንሰሳት ሀብት ተጠሪ ፅህፈት ቤት የእስሳት በሽታ ቅኝት ባለሙያ አቶ ዘላለም ይታየው÷ መንስዔው በትክክል ይህ ነው ባይባልም በእርግዝናዎቹ የመጀመሪያ 36 ሰዓታት በተወሰደ መድሃኒት አልያም ከእናትና አባት በተቀበለችው ጅን ምክንያት ሊከሰት ይችላል ነው ያሉት።
በጎቹ ከሚመገቡት መኖ ጋር ኬሚካል ከተመገቡም ይህን አይነት ፍጥረት ሊገጥም ይችላል ያሉ ሲሆን ባለሙያው በዞኑ ከዚህ በፊት 5 እግሮች ያሏት በግ መወለዷን አስታውሰዋል፡፡
በአበበ የሸዋልዑል
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
90,611
People Reached
17,860
Engagements
Boost Post
2K
435 Comments
275 Shares
Like
Comment
Share