የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም ቱሪዝም ቀን በሲዳማ ክልል ይከበራል

By Alemayehu Geremew

September 21, 2021

አዲስ አበባ፣መስከረም 11 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት የዓለም ቱሪዝም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ መስከረም 17 በሲዳማ ክልል ይከበራል፡፡

በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ ‘’ቱሪዝም ለሁለንተናዊ እድገት’’ በሚል መርህ የባሕላዊ ፣ታሪካዊ፣ሰዉ ሰራሽና ተፈጥሯዊ መስህብ ሐብቶች ጉብኝት የሚደረግ ሲሆን፥ በዓሉ በተጨማሪም በስፖርታዊ ዉድድር እንዲሁም በኤግዚቢሽንና ሲምፖዚየም ከመስከረም 12 ቀን 2014 ጀምሮ በሃዋሳና አካባቢዉ እንደሚከበር ከባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡