Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ ያሉ የወረባቦ ወረዳ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጁንታው እያደረሰ ያለውን ጥፈት ለመከላከልና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር መከላላከያን መቀላቀል ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት ያሉት ወጣቶቹ የሀገር ህልውናን ለመጠበቅ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡
የሃይማኖት አባቶች ሲገደሉ፣ እናቶች እና ህጻናት ሲደፈሩ መመልከታችን ሀገርን ከጥፋት ለመታደግ መዝመት እንዳለብን እንድናምን አድርጎናል ያሉት ወጣቶቹ÷ ለሀገር ህልውና ዘብ ለመቆም መዝመት ግዴታ ነው ብለዋል፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ የመጣውን ተቋም ወጣቶቹ መቀላቀላቸው የሚበረታታ ተግር መሆኑን÷ በሽኝቱ ላይ የተገኙት የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሻምበል መሀመድ ገልፀዋል፡፡
ነገ ጄኔራል ለመሆን ዛሬ ወታደር መሆን ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሻምበል÷ ወጣቶቹ ለሀገር መከታ እንዲሆኑ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version