Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኮንትሮባንድ የገባ 4 ሺህ 824 ስቴካ ሺሻ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንትሮባንድ ከውጭ ገብቶ ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ የነበረ 4 ሺህ 824 ስቴካ ሺሻ መያዙን የአዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ሺሻው በቁጥጥር ስር የዋለው በሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-87637 (ኢት) ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ በኮንትሮባንዲስቶች ተጭኖ ትናንት ሌሊት ጨለማን ተገን በማድረግ ለማሳለፍ ሲሞከር መሆኑን በጽህፈት ቤቱ የኮንትሮባንድ መከላከል ቡድን መሪ ኢንስፔክተር አለሙ ይመር ለኢዜአ ገልጸዋል።
ከአራት ሚሊየን 800 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ሺሻ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በአፋር ክልል አሚባራ ወረዳ ልዩ ቦታው ግምጃ ቤት አካባቢ ሊደረሰበት እንደቻለ አስታውቀዋል።
ይህንን የኮንትሮባንድ እቃ ለመቆጣጠር የቅርጫፍ ጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች ከምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ዲቪዥን ሻለቃ ሁለት እና ከፌዴራል ፖሊስ የኮንትሮባንድ መከላከል ዲቪዥን አባላት ጋር የተቀናጀ ተሳትፎ ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡
ሺሻውን ሲያጓጉዙ የተገኙ አሽከርካሪውና ረዳቱ በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ክስ ለመመስረት በሂደት ላይ መሆኑንም ኢንስፔክተር አለሙ ተናግረዋል።
በቀጣይም ከህብረተሰባችን ለሚመጡ ጥቆማዎች ትኩረት በመስጠት ህገ ወጦችን የማደኑ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናልም ነው ያሉት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version