አዲስ አበባ ፣መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ ቦዛ ቀበሌዎች በሽብር ቡድኑ በግፍ የተጨፈጨፉ ንጹሃን ዜጎችን ለማሰብ በደባርቅ ከተማ የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ተካሂዷል።
በስነ ስርዓቱ የደባርቅ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሰላምይሁን ሙላትን ጨምሮ፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ወጣቶች እና የተጎጂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
አቶ ሰላም ይሁን የሽብር ቡድኑ ህወሓት ደባርቅና አካባቢዋን ለመቆጣጠር የነበረው ህልም በግንባሩ በተሰማራው መከላከያ ሰራዊት፣የክልል ልዩ ሃይሎች፣ሚሊሻ እና ፋኖ መክሸፍን አውስተዋል።
ይሁን እጅ ቡድኑ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ ቦዛ ቀበሌዎችን ጨምሮ ሰርጎ ገብቶባቸው በነበሩ አካባቢዎች ህጻናትእና እናቶችን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን ዜጎችን በግፍ ጨፍጭፏል ነው ያሉት።
ለተጎጅ ቤተሰቦች መጽናናትን የተመኙት አስተዳዳሪው የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ ሁሉም ዜጋ በቅንጅት መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።
ተጎጂ ቤተሰቦችን ለማቋቋም እርዳታ ሰጭ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በመላኩ ገድፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!