አዲስ አበባ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ብሄራዊ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ለሁለተኛ ዙር ተመልምለው የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው።
ወጣቶቹ ከዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ተመልምለው የሀገርን ህልውና ለመጠበቅ በፍቃዳቸው ተቋሙን ለመቀላቀል የወሰኑ ናቸው፡፡
ወጣቾቹ ወደ ሀገር መከላከያ ሰራዊት የአሸኛሸት ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር አህመዲን መሀመድ ለወጣቶቹ ባስተላለፉት መልዕክት፥ኢትዮጵያን ለመበተን ጦርነት የከፈተውን አሸባሪውን ህወሀት አስወግዳችሁ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ሃላፊነት ተጥሎባችኋል ብለዋል፡፡
ስልጠናችሁን አጠናቃችሁ ከሌሎች ወንድሞቻችሁ ጋር ተባብራችሁ እትዮጵያን ታፍራና ተክብራ የምትኖር ሀገር እንድምታደርጉ አልጠራጠርም ብለዋል ሚኒስትር ደኤታው።
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረ ጻዲቅ፥ መከላከያን ስትቀላቀሉ የሀገርን ሉዓላዊነትና ክብርን ከማስጠበቅ ባሻገር የልዩ ሙያ ባለቤት የሚያደርጋችሁ በመሆኑ ልትኮሩ ይገባል ብለዋል።
አባቶቻችን ኢትዮጵያን ከነክብሯ እንዳስረከቡን ሁሉ፥ እናንት ወጣቶችም ሀገራችንን ሊዋርድና ዝቅ ሊያደርግ ያሰበውን ጠላት በመደምሰስ ታሪክ ልትሰሩና ህዝባችሁን ልታኮሩት ይገባል ነው ያሉት ።
በአላዩ ገረመው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!