Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በደቡብ ጎንደር አሸባሪው ቡድን ባደረሰው ጥፋት መብራት ተቋርጦባቸው የነበሩ አካባቢዎች አገልግሎት ማግኘት ጀመሩ

 

አዲስ አበባ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ጎንደር ዞን በአሸባሪው ቡድን በደረሰ ውድመት መብራት ተቋርጦባቸው የነበሩ አከባቢዎች አሁን ላይ ኃይል እያገኙ እንደሆነ የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ገለጸ፡፡

የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ማህተቤ አለሙ ለፋና ብሮድካስቲን ኮርፓሬት እንደተናገሩት÷ አሸባሪው ቡድን በዞኑ በሚገኙ ጋሳይ፣ ክምር ድንጋይ፣ እስቴ፣ እንዳቤት እና ጃራገዶ አካባቢዎች ባደረሰው ጥፋት የመብራት አገልግሎት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፥ በተቋሙ ሰራተኞች ርብርብ መጠገን ተችሏል ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ በመብራት ማስተላለፊያ ብሬከር ላይ ባደረስው ጥቃት መብራት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በሰሜን ምዕራብ ሪጅን ሰራተኛች ርብርብ አካባቢዎቹ አሁን ላይ የ24 ሰዓት ኤሌክትሪክ አገልግሎት እያገኙ ነው ተብሏል።

ቡድኑ ያደረሠው ጥፋት እሰከ 2 ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ የሚደርስ መሆኑም ተገለጿል።

ከድር መሐመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version