Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የግሸን ደብረ ከርቤ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ተደርጓል- የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳር

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የዘንድሮው የግሸን ደብረ ከርቤ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ፡፡

የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ሰይድ መሀመድ÷ በተለይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ግብረ ሀይል ተቋቋሞ ወደ ስራ ተገብቷል።

የውሃ ፣የመንገድ ፣የጤና እንዲሁም የጸጥታ ሂደቱ የተሻለ እንዲሆን ተሰርቷል ያሉት አቶ ሰይድ እንደወትሮው ሁሉ በዓሉ በድምቀት ይከበራል ብለዋል።

በጁንታው የተሳሳተ መረጃ አካባቢው ሠላም አለመሆኑ የሚነዛ ቢሆንም የዞኑ አስተዳዳር ልኡካን ቡድን በቦታው በመገኘት ለበዓሉ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ተመልክቷል ብለዋል አቶ ሰይድ።

አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በዓሉ በተሻለ መልኩ እንዲከበር ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ያሉት አቶ ሰይድ ምዕመኑ ወደ አከባቢው በመምጣት በዓሉን እንዲያከብሩም ጥሪ አቅርበዋል።

በአዓሉ ሲከበር ሰርጎ ገቦችን በመለየት ሰለማዊ ሂደት እንዲኖር የጸጥታ ሀይሉ ከሚያደርገው ጥረት ባሻገር ማህበረሰቡም ሀላፊነቱን እዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

በከድር መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version