አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ የክቡር ዶክተሬት ሰጥቷል፡፡
በእውቅና ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት ኦባንግ ሜቶ ሽልማቱ ከጎኔ አብረውኝ ለነበሩ እና ለመላው ኢትዮጵያውያን ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መገኛ እንደሆነች የተናገሩት ክቡር ዶ/ር ኦባንግ ሜቶ፥ ባለፉት ጊዜያት ከነበረው ከፋፋይ ስርዓት በመላቀቅ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ወደ አንድነት እንዲመጡ ምክረ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በውስጥም በውጭም የሚደርስባትን ጫና ተቋቁማ የጀመረችውን የልማት እና የዲሞክራሲ ግንባታ ስርዓት እንደምታጠናክር ዶ/ር ኦባንግ ገልፀዋል፡፡
ወደ ትክክለኛ ማንነታችን እንመለስ ያሉት ኦባንግ ሜቶ የአባይ ምንጭ መገኛ የሆንን የተጋመድን ወንድማማች ህዝቦች ነን፡፡
የስልጣኔ፣ የአንድነት፣ የሰብዓዊነት እና የመተባበር ኢትዮጵያዊነት ከፍታ ላይ እንቀመጥ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል::
ተመራቂ ተማሪዎችም ተመርቀው ከወጡ በሁዋላ የሃገሪቱን አንድነት ለመጠበቅ በሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!