የሀገር ውስጥ ዜና

በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ውጤታማ የስራ አፈፃጸም ለነበራቸው የሠራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጠ

By Feven Bishaw

September 17, 2021

አዲስ አበባ ፣መስከረም 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ውጤታማ የስራ አፈፃጸም ለነበራቸውና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የሠራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጠ፡፡

በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የፋናንስ ስራ አመራር ዳይሬክተር እና የዋና መምሪያው ተወካይ ብርጋዴር ጄኔራል ደረጀ መገርሳ ÷ መንግስት በሠራዊቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የሰራዊቱን መብት ለማክበር ትኩረት በመስጠት በተለየ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡