ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሦሥቱ የቻይና ጠፈርተኞች ተልዕኳቸውን አጠናቀው ተመለሱ

By Alemayehu Geremew

September 17, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኅዋ ጣቢያ ግንባታ ወደ ጠፈር የተላኩት ሦስቱ የቻይና ጠፈርተኞች የ 3 ወር ተልዕኳቸውን አጠናቀው በዛሬው ዕለት ወደ ምድር ተመለሱ፡፡

ወደ ጠፈር የተላኩት ኒ ሀይሼንግ ፣ ሊዩ ቦሚንግ እና ታንግ ሁንጉቦ የተባሉ የጠፈር ተመራማሪዎች ሲሆኑ ÷ የተመለሱበት የጠፈር መንኩራኩር ሼንዙ - 12 እንደሚባል ተጠቁሟል፡፡

መንኮራኩሩ በሰሜን ቻይና ሞንጎሊያ ራስ ግዛት ዶንግፌንግ ማረፊያ ጣቢያ በሠላም መድረሱም ነው የታወቀው።

ሦስቱ ጠፈርተኞች ወደ  ኅዋ የተላኩት በፈረንጆቹ ሰኔ 17, 2021 ሲሆን፣ በቆይታቸው በቀን ሁለት ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሢሠሩ ነበርም ተብሏል፡፡

የጠፈር ቆይታው በቻይና የኅዋ ምርምር ታሪክ ረጅሙ ቆይታ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ምንጭ ÷ ሲጂቲ ኤን