አዲስ አበባ ፣መስከረም 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል “የነጩ ፖስት ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዛሬው እለት ተካሂዷል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ዘመቻውን ባስጀመሩበት ወቅት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው አሸባሪው የህወሓት ቡድን በተለይም በአሁኑ ወቅት የአማራ እና አፋር ክልል ህዝቦች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።