አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ወሎ ዞን ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በወረባቦና በተሁለደሬ ወረዳዎች በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ጉዳት ለደረሰባችው ወገኖች ድጋፍ አደረገ።
ጽሕፈት ቤቱ 1ሺህ ኩንታል ዱቄት፣ 2 ሺህ ሊትር ዘይት፣ 4 ኩንታል የሕጻናት አልሚ ምግብ እና 1 ሺህ ብርድ ልብስ ነው ለተጎጂዎቹ ድጋፍ ያደረገው፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሳይ ማሩ ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!