የሀገር ውስጥ ዜና

የድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ውል ለሶስት ወራት ተራዘመ

By Meseret Awoke

September 16, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶችን ለሶስት ወራት ውላቸው እንዲራዘም ወሰነ፡፡

የድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶችን ከመስከረም 4፣2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት እስከ ታህሳስ 3፣2014 ዓ.ም ነው የተራዘመው፡፡

በመዲናዋ ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ወደስራ ከገቡ በኋላ በአማካይ 392 አውቶቡሶች በየቀኑ አገልግሎት እንዲሰጡ በመደረጉ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

በሁሉም አውቶቡሶች ላይ GPS በመግጠም የክትትልና ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን ይህም በቀን በአማካኝ ለ182 ሺህ ተጠቃሚዎች አገልግሎት በመስጠት የተሳፋሪ የጊዜ ቆይታን በአማካይ ከ60 ደቂቃ ወደ 12 ደቂቃ ዝቅ በማድረግ አገልግሎት አሰጣጡም እየተሻሻለ መጥቷል፡፡

ማህበራትም በውሉ መሰረት የተቀመጡ የአሰራር ስርዓቶችን ስራ ላይ በማዋል ከዚህ የተሻለ አገልግሎት እንዲኖር ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አሳስቧል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከጥቅምት 9፣2013 ዓ.ም ጀምሮ ሀገር አቋራጭ አውቶቡሶች በኪራይ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ከከተማው ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!