አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ6 ዓመቱ ህጻን ካታሪያ ለትምህርቱ በነበረው ፈጣን አቀባበል እና በቤተሰቦቹ እገዛ በእድሜ ትንሹ ፕሮግራመር በመሆን አዲስ ክብረወሰን አስመዝግቧል፡፡
ታዳጊው አይ ቢ ኤም በሚያዘጋጀው የኦንላይን የሶፍትዌር ደቨሎፒንግ የክህሎት የስልጠና ኔትወርክ ውስጥ በመግባት የኮምፒውተር ፕሮግራም ስልጠናዎችን ለተከታታይ ወራት መውሰዱ ተገልጿል፡፡
የአይ ቢ ኤም ብሎግ ፖስት እንደዘገበው÷ ታዳጊው ድርጅቱ በሚያዘጋጀው የኦንላይን የሶፍትዌር ደቨሎፒንግ የክህሎት ስልጠና አምስት የተለያዩ የትምህርት አይነቶችን አጠናቆ በመማር ፓይተን በተባለው የኮምፒተር ፕሮግራም የሰርተፍኬት ዲግሪ ሊያገኝ ችሏል፡፡
በየትኛውም የእድሜ ደረጃ ለሚገኙና የኮምፒውተር ፕሮግራም ለመማር የሚፈልጉ ሰዎች በሚሳተፉበት በዚህ የአይ ቢ ኤም የትምህርት እድል ላይ የተሳተፈው ይህ ታዳጊ በተለይም የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ የትምህርት ዘርፍ ላይ ለመስራት የሚያስችለውን የኮምፒውተር ፕሮግራም አጥንቷል ነው የተባለው፡፡
እንግሊዝ ውስጥ በምትገኘው ኖርዝሃምፕተን የተወለደው ካታሪያ÷ ከብዙ ወራት ትምህርት በኋላ በእድሜ ትንሹ ፕሮግራመር በመሆን በጊነስ የአለም ክብረወሰን ስሙ ሊመዘግብ ችሏል፡፡
ታዳጊው በቤተሰቦቹ የተደረገለት የቁሳቁስ ድጋፍ እና የተሰጠው የትምህርት እድል ለእዚህ እንዳበቃው ገልፆ÷ የኮዲንግ ትምህርትንና ስልጠናዎቹን ያለመሰልቸት መማሩም ለጥሩ ውጤት እንዳበቃው አስረድቷል፡፡
ሌሎች ታዳጊ ልጆች የኮምፒውተር ፕሮግራም ስልጠናዎችን በሚወስውዱበት ሰዓት ራሳቸውን እያዝናኑ ሊሚሩ እንደሚገባ ያስረዳው ታዳጊው÷ ወደፊትም በኮግኒቲቭ የኮምፒውቲንግ መስክ ላይ ትልልቅ ስራዎችን መስራት እንደሚፈልግ ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!