የሀገር ውስጥ ዜና

የመራጮች መዝገብ ይፋ ማድረጊያና የአቤቱታ ማቅረቢያ ግዜ መስከረም 12 ቀን ይጠናቀቃል

By Feven Bishaw

September 16, 2021

አዲስ አበባ ፣መስከረም 6፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድየመራጮች መዝገብ ይፋ ማድረጊያ እና የአቤቱታ ማቅረቢያ ግዜ መስከረም 12 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ፡፡

6ኛው አገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው በደቡብ፣ ሶማሌና ሃረሪ ክልሎች ምርጫው መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡