የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከሮታሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት እና ከኢንተርፒስ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

September 15, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከሮታሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ሸክሃር ሜታ እና ከኢንተርፒስ ፕሬዚዳንት ስኮት ዌበር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ ከሮታሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ጋር ባደረጉት ውይይት ለኮቪድ -19 በሚያስፈልግ ድጋፍ፣ ትምህርትን በማዳረስ፣ የአካባቢ ንፅህናን በማሻሻል እና የሴቶችን አቅም በማጎልበት ዙሪያ ባሉ የሮታሪ ኢንተርናሽናል ፕሮግራሞች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ሮታሪ ኢንተርናሽናል ለኢትዮጵያ ሮታሪ ክለቦች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይም ድርጅቱ ተጨማሪ ፕሮጀክቶች ላይ እንዲሰማሩ መጋበዛቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ ፕሬዚዳንቷ ከኢንተርፒስ ፕሬዚዳንት ጋ ባደረጉት ቆይታ በኢትዮጵያ ባሏቸው የሰላም ግንባታ እና ዘላቂ የማድረግ ፕሮጀክቶቻቸው ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ዘለቄታዊ ሰላም ሊመጣ የሚችለው በህዝብ እንደሆነ የገለጹት ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ÷ በአካባቢ ደረጃ የሽምግልና እና የሰላም ግንባታ ጥረቶችን እውን ለማድረግ እንዲረዳ የሴቶችን ሚና በማሳደግ ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!