አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የተጋረጠባትን የህልውና አደጋ ለመታደግ ወጣቶች የሃገር መከላከያ ሠራዊትን መቀላቀል እንደሚገባቸው ብርጋዴር ጄነራል አዳምነህ መንግሥቴ ገልጸዋል።
ብርጋዴር ጄነራል አዳምነህ መንግሥቴ እንደተናገሩት÷ የሃገር መከላከያ ሠራዊት መቀላቀል የተከበረና የላቀ የሙያ ባለቤት የሚያደርግ ነው።
ወጣቶች በተለያየ የሙያ ዘርፍ እንደሚሰማሩት ሁሉ በውትድርናው ዘርፍም የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ማለታቸውን የዘገበው አሚኮ ነው።
‘’ወጣቱ ወደ መከላከያ ሠራዊት ቢቀላቀል የሚፈልገውን ዓላማ ለማሳካትም ሆነ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ለመላመድ ይጠቅመዋል፤ ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ጋር አብሮ በመሥራት የተለያዩ ተሞክሮዎችን መቅሰም ያስችላል ነው’’ ያሉት።
በተጨማሪም ወጣቱ የውትድርና ሙያን ካልተቀላቀለ ሀገርን ለማፍረስ ከውስጥም ሆነ ከውጪ ሊመጡ ለሚችሉ ኃይሎች ተገዢ ለመሆን በር ይከፍታል ያሉ ሲሆን÷ ኢትዮጵያ የራሷን ታሪክ ጠብቃ፣ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር የማድረግ ግዴታም ጭምር እንዳለበት ነው ብርጋዴር ጄነራል አዳምነህ የተናገሩት።
ወጣቱ ይህን እንዳያደርግ ተላላኪዎች ስላሉ ተላላኪዎችን በአጭሩ ማስቀረት እንደሚጠበቅ አሳስበው÷ ጠላትን ለመከላከልና የሃገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የሃገር መከላከያ ሠራዊት መቀላቀል ወሳኝ ነው ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን