Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከአንዲት ታካሚ 20 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ በቀዶ ጥገና ተወገደ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኦቶና ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ከአንዲት እናት 20 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ በተሳካ ቀዶ ጥገና መወገዱ ተሰማ፡፡

ታካሚዋ በሰባት ወራቸው ለእርግዝና ክትትል በመጡበት በማህፀናቸው እጢ መኖሩን ማወቃቸው የተገለፀ ሲሆን÷ የህክምና ባለሙያዎች ለፅንሱ ደህንነት ሲባል ከወሊድ በኋላ ህክምና ለመስጠት መወሰናቸው ተነግሯል።

ታካሚዋ በመጀመሪያ እርግዝናቸው ወቅት ምንም አይነት ችግር እንደሌለ ተናግረው÷ ነገር ግን በሁለተኛው እርግዝና ወቅት ለክትትል በመጡበት በሰባት ወራቸው ዶክተሮች በማህፀናቸው እጢ መኖሩን እንደነገሯቸውና ስጋት እንዳደረባቸው ገልፀዋል።

ሁለተኛ ልጃቸውን በሰላም ከተገላገሉ በኋላም ዶክተሮች የሰጧቸውን ቀነ ቀጠሮ በመጠባበቅ ላይ ሳሉ የተለየ ህመም ስለተሰማቸው በአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል መጥተዋል።

ዶክተሮችም በተሳካ ሁኔታ ከሆዳቸው 20 ኪሎግራም የሚመዝን እጢ ያወጡ ሲሆን÷ አሁን ላይ ታካሚዋ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ኦቶና ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል በእናቶችና ህፃናት ክፍል የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር በላቸው ሾቴ÷ በርካታ እናቶች በአሁኑ ጊዜ ለጤናቸው ትኩረት በመስጠት የጤና ተቋማት ጉብኝታቸውን ቢያሻሽሉም አሁንም ይቀራል ብለዋል፡፡

በመለሰ ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version