አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ የሚገኙ ወርቅ እና ብር ሰሪዎች ማህበር እና የፅህፈት መሣሪያ መደብር ባለቤቶች ለሀገር መከላከያ የሠራዊት አባላት ወሎ ግንባር ተገኝተው ድጋፍ አደረጉ።
አቶ አበበ ገብረ መስቀል የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በወቅቱ እንደተናገሩት፥ ማህበረሠቡ ለሠራዊቱ ደጀንነቱን በተለያየ መንገድ እያስመረከረ ነዉ ብለዋል።
በዚህም እስካሁን ለ10ኛ ዙር ልዩ ልዩ ድጋፎች በተለያዩ ግንባሮች መደረጋቸውን ተናግረዋል።
አቶ አበበ ገብረመስቀል አያይዘውም ጁንታው ባለበት ቦታ እስኪቀበር ድረስ ለሠራዊታችን ተመሣሣይ የደጀንነት ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት ለጦር ጉዳተኞች አገልግሎት የሚውል በርካታ ቁጥር ያላቸው ነጠላ ጫማዎች ፣ጁስ ፣ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ እና ውሃ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ፥ በተመሣሣይ ወሎ ግንባር ሊብሶ ደግሞ የእርድ በጎች እና እሽግ ውሃ ድጋፍ አድርገዋል።
የወርቅና ብር ሠሪዎች ማህበር እና የፅህፈት መሣሪያ መሸጫ ማህበራት ተመሣሣይ የደጀንነት ተግባራትን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
እሸቱ ወ/ሚካኤል
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
61
Engagements
Boost Post
59
1 Comment
1 Share
Like
Comment
Share