Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጳጉሜን መጨረሻ የድል ቃል ኪዳን ብስራት ቀን በደማቅ ሥነ ስርዓት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ ወጣቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት አዲስ አበባ ተከብሯል፡፡
በመርሐ ግብሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማህበራዊ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
አቶ ጃንጥራር አምስቱም የጳጉሜ ቀናት ሁሉም የሚዘመሩ ናቸው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያዊነት ዘላለማዊነት ነው፣ አገልጋይነትም የዘውትር ሥራ ነው፣ መልካምነትም ሁል ጊዜ ዓመቱን ሙሉ አብረውን ያሉና ሁሌ ልንተግብራቸው የሚገቡ ተግባራት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የድል ብስራት ቀንን ስናከብር ብዙ ድሎችን ፈጽመናል ያሉት አቶ ጃንጥራር÷ ነገም እንደምንፈጽም ዛሬ ላይ ሆነን ቃል እንገባለን ማለታቸውን ከአዲ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመጪው አዲስ ዓመትም የከተማዋን ሁለንተናዊ እድገት ያማከሉ እና ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት ላይ እንደሚሰራ አቶ ጃንጥራር አመላክታዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version