የሀገር ውስጥ ዜና

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የአዲስ ዓመት የእርድ ቆዳን ለህልውና ዘመቻ ለመሰጠት ወሰኑ

By Meseret Awoke

September 09, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የአዲስ ዓመት የእርድ ቆዳን ለህልውና ዘመቻ ለመሰጠት ወሰኑ።

የከተማ አስተዳደሩ ከቆዳና ሌጦ አቅራቢዎች ጋር ባዳረገው ውይይት በህልውና ዘመቻው እየተሳተፉ ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ድጋፍ እንዲሆን በዘመን መለወጫ ዕለት በየቤቱ የሚታረደው የቁም እንስሳት ቆዳ እንዲሰጥ ስምምነት ላይ መደረሱን የከንቲባው የህዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት አማካሪ አቶ አዝመራው ተዘራ ገልጸዋል።

የከተማው ማህበረሰብም ከአሁን ቀደም በተለያየ መልኩ ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው÷ አሁንም የጠላት ሀይል ሙሉ በሙሉ እስኪፀዳ ድረስ ድጋፍ ስለሚያስፈልግ በግንባር ለሚዋደቁት ጀግኖች ለበዓል የሚያርደውን እንስሳት ቆዳ ድጋፍ በማድረግ ሊደግመው እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የተደረሰውን ስምምነት ለከተማው ማህበረሰብ የማስገንዘብ ስራ እየተሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ በእርድ ወቅት ህብረተሰቡ ለቆዳ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

ህብረተሰቡም ወደ ቆዳ አቅራቢዎች ቆዳ ይዞ ሲሄድ ህጋዊነቱን ለማረጋገጥ ኩፓን ይሰጠዋል ያሉት አቶ አዝመራው÷ ቆዳ ከተሰበሰበ በኃላ ተሾጦ ገንዘቡ ለህልውና ዘመቻው ይውላል ተብሏል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!