Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ የሴካፋ ውድድርን 2ተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬኒያ ናይሮቢ ሲካሄድ በሰነበተው የምስራቅና የመካከለኛው አፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና (ሴካፋ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በኬኒያ አቻው ተሸንፎ 2ተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡
በዚሁ መሠረት ዛሬ ከቀኑ 10፡00 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ከኬኒያው ቬጋ ኩዊንስ ጋር ባደረገው የፍጻሜ ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በመሸነፉ የነበረውን የሻፒዮናነት ዕድል አጥቷል፡፡
እስከ መደበኛው ሰዓት 1 አቻ የነበሩት ቡድኖቹ÷ በተጨማሪ ደቂቃ በቅጣት ምት በተቆጠረች ጎል ሊሸነፍ ችሏል፡፡
በዚህም የብር ሜዳሊያ እና የ20 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version