Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳውን አሸባሪ የህወሓት ቡድን እስከ ወዲያኛው እንደመስሰዋለን- ተመራቂ ወታደሮች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት÷ በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን ወታደሮች አስመረቀ።

ተመራቂ ወታደሮቹ በቆይታቸው አስተማማኝ ወታደራዊ ስልጠና ማግኘታቸውን ለኢዜአ ገልፀዋል።

በዚህም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሰሩ የውጭ ኃይሎችንና የውስጥ ከሃዲዎችን ለመመከት ዝግጁ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳውን አሸባሪ የህውሓት ቡድን እስከ ወዲያኛው እንደመስሰዋለን ብለዋል።

በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ የምድር ኃይል ምክትል አዛዥ የሰው ሃብት ልማት ሜጀር ጀኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version