የሀገር ውስጥ ዜና

አረንቻታ ሚዲያ ኮምቦልቻ ለሚገኙ መከላከያ ሰራዊት አባላት ቤተሰቦች ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

September 08, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አረንቻታ ሚዲያ ኮምቦልቻ ለሚገኙ መከላከያ ስራዊት አባላት ቤተሰቦች ለበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ፡፡

ሚዲያው ለበዓል መዋያ ያሰባሰበውን ድጋፍ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ ፣የአማራ ክልል ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ፣ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ፍቅረማርያም ደጀኔ፣ የኮምቦልቻ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር አህመድ የሱፍ፣ ሸህ ሁሴን መሐዲ እና ቆሞስ አባ ተስፋሚካኤለ ደሳለኝ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ቤተሰቦች አስረክበዋል፡፡