Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሽብርተኛው በህዳሴ ግድብ በኩል ተደጋጋሚ ማጥቃት ቢያደርግም አልተሳካለትም – ሌተናል ጀኔራል አስራት ዲኔሮ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሽብርተኛው በህዳሴ ግድብ በኩል ተደጋጋሚ ማጥቃት ቢያደርግም በመከላከያ ሰራዊትና በክልሎች ልዩ ሃይል መደምሰሱን የምድር ሃይል ዋና አዛዥና የመተከል የተቀናጀ ግብረ ሃይል ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል አስራት ዲኔሮ አረጋገጡ ።

በዚህም ውጊያ ላይ ሽብርተኛው የተለያዩ ከቀላል እስከ ከባድ መሳሪያ ፀረ-ተሽከርካሪና ፀረ ሰው ፈንጅዎችንና ተቀጣጣይ ቦንቦችን አስታጥቆ ቢልክም ሰራዊታችን ከክልሎች ልዩ ሃይል ጋር በመጣመር አኩሪ ገድል ፈጽመዋል ፡፡

ሽብርተኛው የላካቸው ቅጥረኞች ከ220 በላይ ሲደመሰሱ ከ70 በላይ ቆስለውበት ቁስለኞችን ይዞ ወደ መጣበት ሸሽቷል ብለዋል ፡፡

ኢትዮጵያ ያለችበትን ችግር የምትወጣው በህብረተሰቡ ድጋፍ ነውና ህብረተሰቡ ፀጉረ ልውጥ ሰዎችን ሲያይ ጥቆማ በመስጠት የጁንታውን ህልም በጋራ ማምከን አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version