አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር እና አማራ ክልሎች ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማት አገልግሎት ለማስጀመር የዳሰሳ ጥናት በዚህ ሳምንት ይጀመራል።
የብሄራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል የሚኒስትሮች ኮሚቴ ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።
ከዕለታዊ የሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ ጎን ለጎን የተጀመሩ የመልሶ ማቋቋም ተግባራትን ለማስቀጠል በጤና፣ በትምህርት፣ በውሃና ኢነርጂ፣ በግብርና፣ በትራንስፖርት፣ በኮንስትራክሽ እና በሌሎች ዘርፎች በአፋር እና አማራ ክልሎች የደረሰውን የጉዳት መጠን በመለየት ተቋማትን አገልግሎት ለማስጀመር የባለሙያዎች ቡድን የዳሰሳ ጥናት ለማካሄድ በዚህ ሳምንት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተመልክቷል።
ተጨማሪ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን የስነልቦና ቀውስ ለማስወገድ የሚረዳ የስነልቦና ባለሙያ ቡድኖች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ የህክምና ቡድኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያስችል አቅጣጫ ተቀምጧል።
በክልሎቹ የሚገኙ የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ማስተባበሪያ ማዕከላትን አቅም ለማጠናከር ተጨማሪ የባለሙያ ቡድኖች እንዲሰማሩ ተደርጓል።
የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ የማቋቋም ተግባራት ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!