አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የአፍሪካ ህብረትና የኢትዮጵያ ዋና ተጠሪ ከሆኑት እሌኒ ካይሩ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ በሚቀጥሉት ዓመታት የከተሞችን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ በተነደፉት ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ላይ መክረዋል፡፡
ኢንጂነር አይሻ በከተሞች ዘርፍ ዋና ዋና ጉዳዮችን በመለየት ፕሮጀክቶች ተነድፈው ወደተግባር ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አውሮፓ ኢንቨስትመንት ዋና ተጠሪዋ በበኩላቸው÷ በተለይም በመኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ በአረንጓዴ ልማትና የከተሞችን የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለማዘመን ተለይተው የተቀረፁ ፕሮጀክቶችን በፋይናንስ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን መግለፃቸውን ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን