Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ በተጓጓዘ የኮንቴነር ጭነት ብዛት እና ባስገኘው ገቢ ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ በተጓጓዘ የኮንቴነር ጭነት ብዛት እና በዘርፉ በመነጨው ገቢ ከአለም የ47ኛ እንዲሁም ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የዓለም አቀፍ የባህር ኃይል ድርጅት(አይ ኤም ኦ) ሪፖርት ማመላከቱን ትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ከ4 ሺህ 500 በላይ ባህረተኞች እንደሚገኙ የተመላከተ ሲሆን፥በባህረተኞች ብዛት ከአፍሪካ የ4ኛ ደረጃ ላይ እንድትገኝ ማስቻሉም ተገልጿል።
ይህም ኢትዮጵያ በዘርፉ እስከ 9 ሚሊየን ዶላር እንድታገኝ አስችሏታልም ነው የተባለው።
ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቱንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ 1 ሺህ 188 ኪ.ሜ አዳዲስ መንገዶች መገንባታቸውንም ገልጿል።
ከአዳዲስ መንገድ ግንባታው ባለፈም በበጀት ዓመቱ 10 ሺህ 813 ኪ.ሜ የመንገድ ጥገና ማከናወኑን አስታውቋል ።
በተጨማሪም በርካታ ሎሌች አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶች መጀመራቸውንም ነው ያመላከተው።
ከዚያም ባለፈ የመንገድ ዘርፉን ሊያሳድጉ የሚችሉ በርካታ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ አሰራሮችና የቴክኖሎጂ ስርዓቶች መዘርጋታቸው ተገልጿል።
በበጀት ዓመቱ በአገር አቋራጭ ትራንስፖርት ስርዓት ከ570 ሚሊየን ህዝብ በላይ መጓጓዙ የተገለጸ ሲሆን፥ ከ32 ሺህ ተሽከርካሪዎች በላይ የፍጥነት መቆጣጠሪያ ማሽን እንደተገጠመላቸው ተመላክቷል።
በአገራችን የትራፊክ ደህንነት በትምህርት ካሪኩለም ውስጥ ተካቶ ከ2014 ጀምሮ ለተማሪዎች እንዲሰጥ ዝግጅት መጠናቀቁም ተገልጿል።
በ10 ሺህ ተሽከርካሪ በ2012 ዓ.ም 34 ነጥብ 3 የነበረው የሞት መጠን በ2013 ወደ 32 ነጥብ 6 መቀነስ መቻሉም ነው የተገለጸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

No photo description available.
0
People Reached
237
Engagements
Distribution Score
Boost Post
215
6 Comments
14 Shares
Like

 

Comment
Share
Exit mobile version