የሀገር ውስጥ ዜና

በወሎ ግንባር ህወሓት ያወደማቸውን መሰረተ ልማቶች በመጠገን የበኩላችን እየተወጣን ነው-የግንባሩ ዕዝ መሃንዲስ መምሪያ

By Melaku Gedif

September 07, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በወሎ ግንባር አሸባሪው ህወሓት ያወደማቸውን የመሰረተ ልማት አውታሮችና ሰራዊቱ ለግዳጅ የሚንቀሳቀስባቸውን የገጠር መንገዶች በመጠገን ለህልውና ዘመቻው የበኩሉን ሃላፊነት እየተወጣ መሆኑን የግንባሩ ዕዝ መሃንዲስ መምሪያ ሃላፊ ተናግረዋል።

መሃንዲስ መምሪያው ሰራዊቱ ለግዳጅ በተሰማራባቸው ቦታዎች ሁሉ ዘልቆ በመግባት ካለው የክረምት ወራት ጋር ተያይዞ በጎርፍ የተበላሹ መንገዶችን እየጠገነ ለተሽከርካሪ ምቹ በማድረግና ጠላት የሚፈጥራቸውን ሰው ሰራሽ መሰናክሎች በማስወገድ እየተመዘገበ ላለው ድል ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል።