የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴኔጋል ገቡ

By Melaku Gedif

September 07, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ሴኔጋል ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሴኔጋል በሚኖራቸው ቆይታም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ጋር በሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡