የሀገር ውስጥ ዜና

ወጣቱ መከላከያ ሰራዊትን በመቀላቀል የሃገርን ህልውና ማስጠበቅ እንዳለበት ተገለጸ

By Meseret Awoke

September 07, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ወደ ሀገር መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀል የሃገርን ህልውና ማስቀጠል እንዳለበት ተገለጸ።

የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ፍስኀ ወልደ ሰንበት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ የገጠማትን የህልውና ስጋት ለመመከት ወጣቱ እያሳየ ያለው ተሳትፎ የሚደነቅ ነው።

ይህን ቁርጠኝነት የበለጠ በማጠናከር የሃገር ህልውና ደጀንነቱን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመው፥ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ወደ ሰራዊቱ መቀላቀል እንደሚገባ አመላክተዋል።

ወጣቱ በጦር ውሎ ያሳየው ጀግንነት ለመከላከያ ሰራዊቱ ተጨማሪ አቅም እንደሆነውም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በጀግናው የመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ አካላት እንዲሁም በህዝቡ እየተመታ እየሸሸ ያለውን የአሸባሪውን ህወሓት ኃይል ግብዓተ መሬት ለመፈጸም መረባረብ አለብን ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሙሉቀን አበበ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!