Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኮቪድ- 19 የዴልታ ዝርያ በኢትዮጵያ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ ዴልታ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ፥ በኢትዮጵያ ባለፉት ሳምንታት በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች፣ የሚሞቱና ፅኑ ህሙማን ቁጥር በጣም አሻቅቧል ብለዋል።
አዲሱ ዝርያ ሁሉንም የዕድሜ ክልል የሚያጠቃ፣ ለከባድ ህመምና ሞት የሚዳርግ በተለይም ባልተከተቡ ሰዎች ላይ የሚበረታ ዝርያ መሆኑን ገልፀዋል።
ክትባት በየጤና ተቋማቱ በመገኘት እንዲወስዱ፣ የኮቪድ ፕሮቶኮልን ከሁሉም ተቋማትና ግለሰቦች እንደሚጠበቅም ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ብቻ 8 ሺህ 300 ሰዎች በወረርሽኙ ሲያዙ እስካሁን በአገሪቱ 313 ሺህ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል።
ከ4 ሺህ 700 በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል።
በኮቪድ ወረርሽኝ የመያዝ ምጣኔውም ከ1 በመቶ ወደ 20 በመቶ አሻቅቧል፤ ባለፈው ሳምንት 118 ሰዎች ሞተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version