አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮና ቫይረስ የተጠቃች እናት ከቫይረሱ ነፃ የሆነች ልጅን በቻይና ሃርቢን ሆስፒታል መገላገሏን የከተማዋ ጤና ኮሚሽን አስታወቀ።
በቫይረሱ ከተጠቃችው እናት የተወለደችው ህጻን 3 ነጥብ 05 ኪሎ ግራም የምትመዝን ሲሆን፥ ከእናቷ ማህጸን ከወጣች ከአንድ እስከ አምስት ደቂቃ ውስጥ ለ10 ጊዜያት ምርመራ ተደርጎላት በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች ተብሏል።
ሆስፒታሉ እንዳስታወቀው ለበርካታ ቀናት በለይቶ ማቆያ በተሰጣቸው ህክምና እና ክትትል እናትና ልጅ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ።
የ38 ዓመቷ እናት በተለያዩ የህክምና ባለሙያዎች ስጋት እንዳይፈጠርባት የምክር አገልግሎት ከሰጧት በኋላ በቀዶ ህክምና ልጇን እንድትወልድ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።
በዚህ ህክምና የተሳተፉ ባለሙያዎች ለቫይረሱ እንዳልተጋለጡ የተገለፀ ሲሆን፥ አሁን ላይም በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ነው ተብሏል።
ምንጭ፦ www.ecns.cn
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!https://t.me/fanatelevision