Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አየር መንገዱ ወደ ሱዳን ያጓጓዘው መሳሪያ ለአደን የሚውልና ተገቢውን የይለፍ ፍቃድ ያሟላ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሱዳን ያጓጓዘው መሳሪያ ለአደን የሚውል ህጋዊና ተገቢውን የይለፍ ፍቃድ ያሟላ መሆኑን አስታወቀ።

የሱዳኑ የዜና ወኪል የሆነው ሱና አየር መንገዱ ባለፈው ቅዳሜ ማታ ወደ ሱዳን ያስገባው መሳሪያ ህገ ወጥ ነው ተብሎ ምርመራ እየተደረገበት ነው ሲል ዘግቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም የዜና ወኪሉ ከሰራው ዘገባ ጋር ተያይዞ ባወጣው መግለጫ፥ መሳሪያዎቹ ለአደን የሚውሉና በህጋዊ መንገድ ስምምነት ተፈጽሞባቸው ወደ ሱዳን እንደተጓጓዙ አስታውቋል።

በመግለጫውም ለአደን የሚውሉት መሳሪያዎቹ በኢትዮጵያ የደህንነት ሃላፊዎች አስፈላጊው ማጣሪያ ተደርጎባቸው ህጋዊ ሂደቱን ተከትለው ወደ ሱዳን መጓጓዘቸውንም ጠቅሷል።

ከዚህ ባለፈም መሳሪያውን ለማጓጓዝ ከሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የይሁንታ ደብዳቤ እንደተሰጠውም ነው የገለጸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version