የሀገር ውስጥ ዜና

የሲዳማ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ ባሕር ዳር ገቡ

By ዮሐንስ ደርበው

September 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል በአሸባሪው የትህነግ ኃይል ወረራ ለተፈጸመበት የአማራ ሕዝብ ያለውን አጋርነት ለመግለጽ ርእሰ መሥተዳድሩ ባሕር ዳር ገብተዋል፡፡

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።