አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ ጳጉሜ 1 ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ፣እዘምራለሁ በሚል መሪ ቃል በመስቀል አደባባይ ለሚደረገው ዝግጅት ከጠዋቱ 11:30 ጀምሮ መርሃ ግብሩ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
.ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ኡራኤል ቤ/ክ . ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኦሎምፒያ . ከሸራተን ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ ሀራምቤ ትራፊክ መብራት . ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ለገሃር ትራፊክ መብራት ላይ . ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ብሄራዊ ቤተ መንግስት .ከተክለሀይማኖት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ብሔራዊ ቲያትር .ከቼርቸል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት .ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ጥላሁን አደባባይ ዝግየሚሆን ሲሆን ለከባድ ተሽከርካሪ ከጎተራ ወደ መስቀልአደባባይ ለሚመጡ መንገዱ አጎና ሲኒማ ላይ የሚዘጋ ይሆናል።
ከዚህም በተጨማሪ በነዚህ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል ።
የተገለጹት መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ መሆናቸው ታውቆ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ እና ሰላም ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎችም እንደሁል ጊዜው የከተማችንን ሰላም ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!