የሀገር ውስጥ ዜና

የዓመቱ  የበጎ ሰው ሽልማት ስነ ስርአት እየተካሄደ ነው

By Meseret Demissu

September 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማት ስነ-ስርዓት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

ለ9ኛ ጊዜ የሚካሄደው የበጎ ሰው ሽልማት ስነ-ስርዓት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ሌሎች ታዳሚዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ለህዝብ እና ለአገራቸው በአርዓያነት የሚጠቀስ ስራ ያከናወኑ ሰዎች ሲሸለሙና ዕውቅና ሲያገኙ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬም ለ9ኛ ጊዜ በሁሉም ዘርፎች ያሸነፉ ዕጩዎች ዕውቅና የሚያገኙ ይሆናል።

በመንግስታዊ ተቋማት ኃላፊነት፣ በቅርስና ባህል፤በማህበራዊ ጥናት፣ በሚዲያና ጋዜጠኝነት፣ ለኢትዮጵያ ዕድገት አስተዋፅዖ ያበረቱ ዳያስፖራዎች እውቅና የሚያገኙ ይሆናል።

በዘንደሮው የበጎ ሰው ሽልማት አንድ ልዩ ተሸላሚ እንዳለ በመርሃ ግብሩ ላይ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል ።

የበጎ ሰው ሽልማት ከተጀመረ  ጀምሮ እስካሁን ለ170 ሰዎች በተለያዩ መስኮች እውቅና መሰጠቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!