አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህውሓት ጥቃት የደረሰበት ከደብረታቦር እስከ ነፋስ መውጫ ከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
መስመሩ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሰታወቀ።
ከደብረታቦር ነፋስ መወወጫ ድረስ ባለው መስመር ላይ በተፈፀመ ጥቃት ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል።
መስመሩን እንደ አዲስ በመቀየርና የተለያዩ መገናኛዎችን በመጠቀም ለመጠገን ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል።
የኃይል ማስተላለፊያው በመጠገን ከትናንት ነሐሴ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽት 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ንፋስ መውጫና ደብረታቦር ከተሞችና አካባቢያቸው ኃይል እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል፡፡
የንፋስ መውጫ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በሽብርተኛው ቡድን ዘረፋና የንብረት ውድመት ቢፈፀምበትም ዳግም በማደስ ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
ምንጭ :- ኢፕድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!