የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ የደን ሽፋኑ 17 በመቶ ደረሰ

By ዮሐንስ ደርበው

September 04, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዓመታት በአካባቢ ጥበቃ ላይ በተሰሩ ስራዎች የሀገሪቷ የደን ሽፋን 17 በመቶ መድረሱን የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ገለፀ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ እንደገለፁት ባለፉት ዓመታት በተፈጥሮ ሀብት ልማትና እንክብካቤ ላይ በተሰሩ ስራዎች የሀገራችን የደን ሽፋን 17 በመቶ ደርሷል።