Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዘመቻችን ወገኖቻችን ከመርዳት እስከ ግንባር ዘመቻ የሚዘልቅ ነው – የአልቡኮ ወርዳ የሣልመኔ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ዘመቻችን ወገኖቻችን ከመርዳት እስከ ግንባር ዘመቻ የሚዘልቅ ነው ሲሉ የአልቡኮ ወርዳ የሣልመኔ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች 37 ኪሎ ሜትር ተጉዘው በደሴ ከተማ ዳውዶ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኙ የተፈናቀሉ ወገኖችን ምሳ አብልተዋል።

በትምህርት ቤቱ ከ800 በላይ ተፈናቃይ ወገኖች ያሉ ሲሆን÷ የእራት ፕሮግራም በመጠለያ ጣቢያው እንደሚኖር የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ እና የገቢዎች ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ይማም ሙህየ ገልጸዋል።

በወረዳው ከ1ነጥብ7 ሚሊየን ብር በላይ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ለአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ድጋፍ አድርገዋል።

ወጣት አሊ ሰይድ በአካባቢያችን በቂ ስልጠና ስለተሠጠን ወገኖቻችንን ከመደገፍ በላይም ከሀገር መከላከያ እናከአማራ ልዩ ሀይል ጋር ተቀላቅለን አሸባሪ ቡድኑን በግንባር እንፋለማለን ብሏል።

ወጣት ሆኖ በአጉል ሱስ ከመናወዝ እራስንና ሀገርን የማዳን ቀን አሁን ነውና መላው የከተማችን ወጣት ለትግል ተነስቷል ነው ያለው።

የከተማው ነዋሪ አቶ በላይ ደምሴ በበኩላቸው÷ ወገንን በፍቅር ማጉረስ ጠላትን ድባቅ መምታት የምናውቅ የአርበኛ ልጆች ነን ብለዋል።
ከዚህ በኋላ ጁንታውን ቤታችን ተቀምጠን የምንጠብቀው ሳይሆን በግንባር የምንፋለምበት ጊዜ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

በአለባቸው አባተ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version