አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ ለመታደግ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን ትተው በጋራ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ኢትዮጵያን ለማዳከምና ለማፈራረስ አሸባሪው ህወሓት ከፊት ቢሰለፍም ከበስተጀርባ ሀገርን ለማዳከም የሚሰሩ የውስጥ ባንዳዎች እና የወጭ ሀይሎች መኖራቸው ተነግሯል፡፡
ኢትዮጵያውያን በዚህ ወቅት በዘር፣ በሃይማኖትና የፖለቲካ ልዩነት ሳያደርጉ በጋራ ሊቆሙ የሚስፈልግበት ጊዜ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸው የፖለቲካ ርዮት ዓለም ልዮነት ሳይገድባቸው ለህልውና ዘመቻ በጋራ ቆመው እየተንቀሳቀሱ ነው መባሉን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያን ህልውና ለመታደግ በፓርቲዎች እየተደረገ ያለው መልካም ጅማሮ በሀገሪቱ ላይ የተጋረጠው ችግር ተቀርፎ ዘላቂ ልማት እስከሚረጋገጥ ድረስ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ነው የተባለው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!