የሀገር ውስጥ ዜና

አንጋፋው ሙዚቃ አቀናባሪ ሻለቃ መላኩ ተገኝ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

By Tibebu Kebede

February 03, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የበርካታ አንጋፋ ሙዚቀኞችን ሙዚቃ ያቀናበረው ሻለቃ መላኩ ተገኝ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ሻለቃ መላኩ ተገኝ ጥላሁን ገሰሰ፣ መሀሙድ አህመድ እና ብዙነሽ በቀለን ጨምሮ የበርካታ አንጋፋ ድምፃውያንን ሙዚቃ ያቀናበረ አንጋፋ የሙዚቃ ሰው ነበር።

ካቀናበራቸው ሙዚቃዎች ውስጥም የጥላሁን ገሰሰ የ13 ወር ፀጋ፣ ምን ታደርጊዋለሽ፣ አታላይ ነሽ እና ይገርማል እንዲሁም የብዙነሽ በቀለ ጭንቅ ጥብብ የሚሉት ሙዚቃዎች ተጠቃሽ ናቸው።

ሻለቃ መላኩ ተገኝ በክቡር ዘበኛ የሙዚቃ ቡድን ውስጥም ለረዥም ጊዜ አገልግሏል።

የሙዚቃው ሰው በተወለደ በ75 ዓመቱም ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

አንጋፋው የዜማ ደራሲ ዓየለ ማሞ ሻለቃ መላኩ ተገኝ አሻራው እስከዛሬ የዘለቀ፣ ዜማን በጥሩ ሁኔታ የሚረዳ እና ብቁ የሙዚቃ ሰው ነበር ሲል ገልፆታል።

የሻለቃ መላኩ ተገኝ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በምስራቅ ፀሃይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision