የሀገር ውስጥ ዜና

82 ዜጎች ከሊባኖስ ወደ አገራቸው ተመለሱ

By Feven Bishaw

September 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) 82 ዜጎች ከሊባኖስ ቤሩት ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ተገለፀ፡፡

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ እና የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራሎች ተወካዮች አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡