የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአንጋፋዉ ድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

By Meseret Awoke

September 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአንጋፋዉ ድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።

ምክትል ከንቲባዋ ‘‘ኢትዮጵያ ታላቅ የጥበብ ሰዉ ነዉ ያጣችው’’ ያሉ ሲሆን÷በአንጋፋዉ ድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ ህልፈተ ህይወት እጅጉን አዝኛለሁ’’ ሲሉ መልዕክታውን አስተላልፈዋል።

’’ ዓለማየሁ እሸቴ ለሚወዳት ኢትዮጵያ በጥበብ ስራዎቹ ብዙ ያደረገ ሃገር ወዳድ ባለሙያ ነበር’’ ሲሉም ነው የገለጹት።

ምክትል ከንቲባዋ አክለውም ‘’በራሴና በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ስም ለቤተሰቦቹ፣ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ለሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ ልባዊ መፅናናትን እመኛለሁ’’ ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!